|| የኅብረት ሥራ ማህበራት በኢትዮጵያ - 2018 ||

የኅብረት ሥራ ማህበራት በኢትዮጵያ፡ አጠቃላይ ሁኔታ

ሰዎች በፈቃደኝነት ላይ ተመስርተው የጋራ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፍላጎቶቻቸውን በጋራ የሚፈቱበት ዘመናዊና ባህላዊ መድረክ።

01. የኅብረት ሥራ ማህበር ምንድን ነው?

የኅብረት ሥራ ማህበር ማለት ሰዎች በፈቃደኝነት ላይ ተመስርተው የጋራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት በጋራ ባለቤትነትና በዲሞክራሲያዊ መንገድ የሚያስተዳድሩት ድርጅት ነው።

"አንድ ለሁሉ፣ ሁሉ ለአንድ!"

የማህበራት አይነቶች በኢትዮጵያ

የግብርና ማህበራት

አርሶ አደሮች ምርታቸውን በጋራ እንዲሸጡና ግብዓቶችን (ማዳበሪያ) በቅናሽ እንዲያገኙ ይረዳሉ።

ቁጠባና ብድር (SACCOs)

አባላት ገንዘብ እንዲቆጥቡና ዝቅተኛ ወለድ ያለው ብድር እንዲያገኙ ያመቻቻሉ።

የሸማቾች ማህበራት

መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን በቀጥታ ከአምራቹ በማምጣት በዝቅተኛ ዋጋ ያቀርባሉ።

የቤት ሥራ ማህበራት

አባላት በጋራ በመቆጠብና በመገንባት የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላሉ።

የእጅ ጥበብና ኢንዱስትሪ

በሽመና፣ በብረታ ብረትና በሌሎች የእጅ ሥራዎች የተሰማሩ ባለሙያዎችን ያቀፋሉ።

02. ሕጎችና መተዳደሪያ ደንቦች

በኢትዮጵያ ማህበራቱ የሚመሩት በ አዋጅ ቁጥር 985/2009 ነው። ዋና ዋና መርሆዎች፡ ዲሞክራሲያዊ ቁጥጥር (አንድ አባል አንድ ድምፅ)፣ ነፃነትና በራስ መተዳደር ናቸው።

አንቀጽ 1፡ ስምና አድራሻ - የማህበሩ መጠሪያና የስራ ቦታ።

አንቀጽ 2፡ ዓላማዎች - ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በጋራ መፍታት።

አንቀጽ 3፡ አባልነት - 18 ዓመትና ከዚያ በላይ።

አንቀጽ 4፡ መብትና ግዴታ - ድምፅ መስጠትና ደንብ ማክበር።

አንቀጽ 5፡ መዋቅር - ጠቅላላ ጉባኤና ስራ አመራር ኮሚቴ።

አንቀጽ 6፡ ትርፍ ክፍፍል - 25% ለሕጋዊ መጠባበቂያ።

  • ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ማሰባሰብ (10-15 ሰዎች)
  • ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄድና ስም መቅረጽ
  • የሥራ አመራር ኮሚቴ መምረጥ
  • መተዳደሪያ ደንብ ማዘጋጀት
  • በኤጀንሲው ቀርቦ የሕጋዊ ሰውነት ማግኘት

03. ቴክኖሎጂና ዲጂታል አሠራር

ከባህላዊ የደብተር አያያዝ ወደ ዲጂታል መሸጋገር ግልጽነትን (Transparency) ይፈጥራል። የሚመከሩ ሶፍትዌሮች፡

  • QuickBooks/Sage: ለአነስተኛ ማህበራት
  • Odoo (ERP): ለትላልቅ ዩኒየኖች
  • Custom Made: በ IFRS መሠረት የተሰሩ
የቴክኖሎጂ ጥቅሞች
✓ ዲጂታል ፋይናንስ (Mobile Banking) ✓ የመረጃ አያያዝ (Cloud Registry) ✓ ኢ-ኮሜርስ (Global Marketing)

04. የሂሳብ አርእስትና የገቢ/ወጪ ሰንጠረዦች

የሂሳብ አርእስት ዝርዝር (Chart of Accounts)
ኮድ አርዕስት ዘርፍ መግለጫ
1000ሀብት (Assets)ወቅታዊበካዝናና ባንክ ያለ ገንዘብ
2000ዕዳ (Liabilities)ወቅታዊየሚከፈል ብድር
3000ካፒታል (Equity)ካፒታልየአባላት ዕጣና ትርፍ
4000ገቢ (Income)ገቢየሽያጭና አገልግሎት
5000ወጪ (Expenses)ወጪደመወዝ፣ ኪራይና ሌሎች
የገቢና ወጪ መመዝገቢያ (Excel Sample)
ቀን መግለጫ ዘርፍ ገቢ (ETB) ወጪ (ETB) ቀሪ
01/06/2016ከዕጣ ሽያጭካፒታል50,000050,000
05/06/2016ለቢሮ ኪራይአስተዳደር05,00045,000
10/06/2016ከምርት ሽያጭሽያጭ20,000065,000

05. ኦዲት፣ ታክስና የትርፍ ክፍፍል

የኦዲት ምርመራ

የሰነድ ምርመራ፣ የንብረት ቆጠራ፣ የባንክ ማስታረቂያና ሪፖርት ማቅረብን ያካትታል።

የግብር (Tax) ሕግ

ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት ቢኖርም፣ የሠራተኞች ደመወዝ ግብርና የቫት (VAT) ግዴታዎች አሉ።

የትርፍ ክፍፍል (Dividend) አሰላለፍ

25% ለሕጋዊ መጠባበቂያ (Legal Reserve) መቀመጥ አለበት። ቀሪው 75% ለአባላት ይከፋፈላል።

የአባል ትርፍ = (አባሉ ያለው ዕጣ / ጠቅላላ ዕጣ) × ትርፍ

ሙያዊ የምክር አገልግሎት (Consultation)

የማህበርዎን መተዳደሪያ ደንብ ለማርቀቅ፣ የሥራ ዕቅድ ለማዘጋጀት ወይም ዲጂታል ሶፍትዌር ለመዘርጋት ዝግጁ ነን።

ባለሙያ፡ ኤፍሬም ገበየሁ (Ephrem Gebeyheu)

ስልክ፡ +251 90 917 3333

[email protected]